Ethio

Friday, 21 June 2019

ኢራን የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላን ላይ ጥቃት ፈፀመች

ኢራን በአየር ክልሏ ቅኝት ስታደርግ በነበረች የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላን ላይ ጥቃት ፈፀመች
 የኢራን ወታደራዊ  ሃይል በሀገሪቱ አየር ክልል ውስጥ ስትንቀሳቀስ በነበረችን የአሜሪካ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላን ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል።
የኢራን አብዮት ዘብ ጠባቂ ወታደሮች በሀገሪቱ የአየር ክልል ውስጥ ቅኝት ስታደርግ በነበረች የዋሽንግተን የስላለ እውሮፕላንን መትተው መጣላቸው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ወታደሮቹ ጥቃቱን የፈፀሙትም በኢራን ደቡብ ሃረሞዝጋን ግዛት ኩህሞባራክ ተብሎ በሚጠራ  አካባቢ መሆኑን  ተገልጿል።
የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል በበኩሉ ንብረትነቱ የዋሽንግተን የሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ከኢራን ግዛት በተወነጨፈ ሚሳኤል ተመትቶ መውደቁን አምኗል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋሽንግተን ምንም አይነት የስለላ አውሮፕላን በኢራን አየር ክልል ውስጥ አለማንቀሳቀሷን ተናግረዋል።
ኢራን በቅርቡ በኦማን ባህረ ሰላጤ ነዳጅ በጫኑ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ አሜሪካ ተጨማሪ 1ሺህ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ የምታሰማራ መሆኑን አስታውቃለች።
አሜሪካ ይህን ውሳኔ ከወሰነች ማግስት ደግሞ ኢራን በአየር ክልሏ ላይ ቅኝት ስታደርግ የነበረችን የስለላ አውሮፓላን  መትታ መጣሏን ገልፃለች።
በሌላ በኩል  ኢራን በኦማን ባህረ ሰላጤ ነዳጅ በጫኑ መርከቦች ላይ ፈፀመች የተባለችውን ጥቃት በማጣጣል
በቀጣዮቹ አስር ቀናት ውስጥ የዩራኒየም ክምችት መጠኗን  ለመጨመር ማቀዷን ይፋ አድርጋለች።
ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ውዝግብ ይበልጥ እንዳያባብሳው ተሰግቷል።